የአፈ-ጉባዔመልዕክት
የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፋ ሲሆን የመድረኩ ዓላማ የቋሚ ኮሚቴዎችን ዕቅድ ከአስፈጻሚ አካላት ጋራ የጋራ ለማድረግ ፣ የበለጠ ለማዳበር እና ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ገልፀዋል።
ባለፋት የምርጫ ዘመን የተቋማት አፈፃፃም ጥሩ እንደነበረ ገልፀው ውይይቱ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን በህግ አወጣጥ ፣ ቁጥጥር እና ውክልናን መወጣት በሚሉት ዙሪያ ላይ ውይይቱ እንዲያተኩር አሳስበዋል።
በተጨማሪም ረቂቅ አዋጆች እንዴት መውጣት አለባቸው ፤ እንዴትስ ማዳበር አለብን እና ወደ ማህበረሰባችን እንዴት እናሳውቅ በሚሉት ዙሪያ መድረኩ ያጠነጠነ እንደሆነ ተናግረዋል። ዕቅዱ ከምክር ቤት ዕቅድ የተቀዳ እንደሆነ አውስተው ቋሚ ኮሚቴው በዕቅዱ ዙሪያ ግልፅ የሆነ ሃሳብ እንዲኖር ለማድረግ እና በጀቱንም አውቆ በተገቢው መንገድ በመምራት ለአስፈፃሚ አካላት ተገቢ ግብረ መልስ እንዲሰጡ የሚያስችል መድረክ ነው ብለዋል።
አቶ ከፊያለው ሙላቴ የግብርና ፣ አካባቢ ጥበቃና የውሃ ሃብት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የቋሚ ኮሚቴውን የጋራ ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን፤ ተሳታፊዎች ዕቅዱ የበለጠ ቢዳብር ያሉት ሃሳቦች ሰጥተው ወይይት ተደርጎበታል።

የተከበሩ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ
ዜናዎች
October 31, 2026
እይታ (0)
ጉባኤው የክልሉን የፍትሕ ሥርዓት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር መልካም ተጽዕኖ ይኖረዋል” ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ...
October 31, 2026
እይታ (0)
የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን መሥራች ጉባኤውን እያካሄደ ነው። “አዲሱ ምክር ቤት የሕዝብ...
October 31, 2026
እይታ (0)
አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኾነው ተሾሙ። የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን...
የቪዲዮ ክምችት
